ዘመናዊ የአማርኛ ቋንቋ እና የኢትዮጵያን ባህል መማርያ ዲቪዲ

ኢትዮጵያ የራሷን ፊደል ለስራና ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ትጠቀማለች። አማርኛ በሀገሪቱ ካሉት ቋንቋዎች ውስጥ ይህንን የኢትዮጵያ ፊደል በተለይ ይጠቀማል።አማርኛ በሴሚቲክ ቋንቋ መደብ ውስጥ በተናጋሪ ብዛት ከአረብኛ ቋንቋ ቀጥሎ በዓለም ሁለተኛ ነው። ብዙ የኢትዮጵያ ስነጹሁፍና የቤተክርስቲያን መጻህፍትም በዚሁ ፊደል የተጻፉ ናቸው።ይህ ዲቪዲም ከሀገራቸው ርቀው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህጻናትና የአማርኛ ቋንቋን ለመማር ለሚፈልጉ ሁሉ ይህን ጥንታዊ ቋንቋ ለማስተማር የተዘጋጀ ነው።ይህ ዲቪዲ ከዚህም በተጨማሪ ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያን ባህል የሚያሳዩ ምስሎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሚገባ ያካተተ ነው። ይህ አሳታፊ ዲቪዲ በሶስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን እነርሱም አማርኛ- እንግሊዘኛ፣ አማርኛ- ፈረንሳይኛ እና አማርኛ- ጀርመንኛ ናቸው።

አማርኛን ለህጻናት ማስተማር ለምን አስፈለገን?

    አማርኛን ቋንቋ በመማር
  • ህጻናቶቻችን ወደፊት ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ባዕድ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል።
  • ህጻናቶቻችን ባህላቸውን እና ታሪካቸውን በራሳቸው ቋንቋ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል።
  • ህጻናቶቻችን ወደፊት በኢትዮጵያ በምርምር፣በንግድ ስራ እና በዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች ረገድ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል።
  • ህጻናቶቻችን ማንነታቸውን እንዲያውቁ ያስችላቸዋል።
  • በማደጎ ልጅነት ከሀገር ውጭ ላሉ ህጻናት የትውልድ ሐገራቸውን ባህል እንዲማሩ ያስችላቸዋል።
  • በኢትዮጵያ ያሉ የውጭ ሐገር ሰዎች ዲፕሎማት ሰራተኞች ወይም የንግድ ስራ ሰዎች በቀላሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለመግባባት ያስችላቸዋል።